in

ጋዜጠኛ ታምራት ነገራ በ50,000 ብር ዋስ እንዲለቀቅ ተወሰነ

[ad_1]

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በጋዜጠኛ ታምራት ነገራ የዋስ ይግባኝ ጥያቄ ላይ ውሳኔ አሳለፈ።

ፍርድ ቤቱ ዛሬ መጋቢት 27 ቀን 2014 ዓ.ም በዋለው ችሎት ጋዜጠኛ ታምራት ነገራ በ50,000 ብር ዋስ እንዲለቀቅ ወስኗል።

የተራራ ኔትዎርክ በይነ-መረብ መገናኛ ብዙሃን ዋና አዘጋጅ የሆነው ጋዜጠኛ ታምራት ነገራ ከታሰረ ዛሬ መቶ 117 ቀናት ቢሆነውም ክስ ሳይመሰረትበትና የዋስ ይግባኝ  ጥያቄውም በጊዜ ቀጠሮ እየተላለፈ ዉሳኔ ሳያገኝ እስከ ዛሬ መቆየቱ ይታወሳል፡፡

ጋዜጠኛ ታምራት ነገራ መጋቢት 1 ቀን 2014 ዓ.ም በገላን ከተማ  ወረዳ ፍርድ ቤት በቀረበበት ወቅት፣ ፍርድ ቤቱ ባስተላለፈው ውሳኔ አቃቤ ህግ በ15 ቀናት ውስጥ ጋዜጠኛው ላይ ክስ እንዲመሰርት ትዕዛዝ ከሰጠ በኋላ ጋዜጠኛው በጠበቃው በኩል መጋቢት 02 ቀን 2014 ዓ.ም   በዋስ እንዲለቀቅ የሚጠይቅ የዋስ መዝገብ ከፍቶ  ነበር፡፡

የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዋስ መዝገቡን ከተመለከተ በኋላ በተለያዩ ጊዜያት ለመጋቢት 08, 13, 15, 20 እና 27 ተለዋጭ ቀጠሮ እየሰጠ ቆይቷል።
በመጨረሻም ዛሬ መጋቢት 27 ቀን 2014 ዓ.ም በዋለው ችሎት ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የጋዜጠኛው የዋስትና መብት እንዲከበርለት ውሳኔ አሳልፏል።



[ad_2]

Source link

What do you think?

Aggregated by Ethiopian News Digest

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

GIPHY App Key not set. Please check settings

በአሜሪካ የህግ መወሰኛ ም/ቤት የቨርሞንት ክፍለ ሃገር ሴኔተር ፓትሪክ ሌሂ በትግራይ ጉዳይ መግለጫ አውጥተዋል።

Kenya Expresses Keenness to Work with Ethiopia in Blue Economy