in

የዎላይታ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ግንባር የዎላይታ ሕዝብ የክልልነት ጥያቄ እንዲመለስ ጠየቀ።

[ad_1]

የዎላይታ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ግንባር የዎላይታ ሕዝብ የክልልነት ጥያቄ እንዲመለስ ጠየቀ።

 

ፓርቲው ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ሰሞኑን ለዎላይታ ህዝብ በይፋ ለውይይት የቀረበው የክላስተር አደረጃጀት ጉዳይ እንዳሳሰበው ገልጿል።

ክላስተሩ የምንታገልለት የዎላይታ ህዝብ እጅግ በጣም በዘመነና በሠለጠነ መንገድ አቅርቦ ህገ መንግስታዊ ምላሽ ሲጠባበቅበት የቆየውን ህገ መንግስታዊ፣ ታሪካዊና ተፈጥሯዊ ራስን በራስ የማስተዳደር የመብት ጥያቄን ወደ ጎን የተወ ነው ያለው የዎላይታ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ግንባር ይህ ድርጊት ህዝቡን ለአያሌ አመታት አላስፈላጊ ዋጋ ሊያስከፍል የሚችልና የህዝቡን ክብርና ህልውና አደጋ ላይ የሚጥል አካሄድ መሆኑን እንዳስተዋለ ተናግሯል።

ይህንን ተከትሎ የፓርቲው ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት በያዝነው ወር መጀመሪያ ላይ አስቸኳይ ስብሰባ በማድረግ ባለ 6 ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥተዋል።

በዚህም መሰረት በሀገሪቱ ሕገ መንግስት መሰረት ሕግ የመተርጎም ሥልጣን የተሰጠው ፌዴሬሽን ምክር ቤት የዎላይታ ህዝብ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምስረታ ህዝበውሳኔ እንዲደራጅ በማድረግ የተጣለበትን ከፍተኛ ኃላፊነትን እንዲወጣ የዎላይታ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ግንባር ጠይቋል።

የፌዴራል መንግስቱም የዎላይታ ህዝብን ጨዋነትና ሠላም ወዳድነት ከግንዛቤ ወስጥ አስገብቶ ህዝቡ ለጠየቀው ህገ-መንግስታዊ የመብት ጥያቄ ኢ-ህገ መንግስታዊ የሆኑ የምላሽ አሰጣጥ ሂደቶችን ባለመከተል በዎላይታና ሌሎች አከባቢዎች በገዢ ፓርቲ ካድሬዎች አመራርነት የተጀመሩ ኢ-ህገ መንግስታዊ የሆኑ የክላስተር አደረጃጀት ውይይቶችን እንዲያስቆም አሳስቧል።

የዎላይታ ህዝብ በተለያዩ ደረጃዎች ባሉ ምክር ቤቶቹ በኩል ወስኖ ካጸደቀው የዎላይታ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አደረጃጀት ውጪ የትኛውም የውዥንብር ሃሳቦች በህዝቡ ዘንድ ምንም ተቀባይነት የሌላቸው በመሆኑ የፌደራሉ መንግስት የዎላይታ ህዝብ መብቱ ተከብሮለት በተሻለ ሁኔታ ሀገሪቱን እንዲያገለግልና እንዲገለገል የማድረግ ሀላፊነቱን በአግባቡ እንዲወጣ መክሯል።

እንዲሁም ከከፍተኛ እስከ ዝቅተኛ ደረጃ ባሉ የመንግስት የአመራር እርከኖች ላይ እያገለገሉ ለሚገኙ የዎላይታ ተወላጆች  “እያንዳንዱ ግለሰብ የሠራው ሥራ ታሪክና ቀጣይ ትውልድ የሚያስታወሰው መሆኑን ተረድታችሁ በዎላይታ ህዝብ ህልውና፣ ክብር፣ የመልማት፣  ዕኩል የማደግና ሁለንተናዊ ከፍታ በራስ የመወሰን ዕድል ላይ የተደቀነውን ክፉ አደጋ የመመከትና የመጋፈጥ ሞራላዊና ታሪካዊ ግዴታ እንዳለባችሁ ተገንዝባችሁ ይህንን ከህገ መንግስት ውጪ የሆነውን ክላስተር የተባለውን አደረጃጀት አምርራችሁ ተቃወሙ” የሚል ጥሪውን አቅርቧል።

ለመላው አባሎቹ፣ ደጋፊዎቹ፣ አጋሮቹና የዎላይታ መጻይ ዕድል ለሚያሳስባቸው ሁሉ ደግሞ የዎላይታ ሕዝብ አላስፈላጊ መስዋዕትነት እንዲከፍልና መንግስታዊ ሽብር ለመፍጠር የታቀደ በሚመስል መልኩ ሆን ተብሎ እየተሸረበ ያለውን ሴራ በንቃትና በጥበብ መከታተል ይጠበቅባችኃል ያለ ሲሆን የፓርቲው መርህ የሆነውን ሠላማዊ ትግል ለማበላሸት ለሚተጉ ኃይሎች ዕድል ፈንታ እንዲነፍጉ አሳስቧል።

ለመላው የዎላይታ ተወላጅ የዲያስፖራ ማህበረሰብም ያላቸውን አንፃራዊ ነፃነት ተጠቅመው የወላይታ ሕዝብ እየደረሰበት ያለውን ኢ-ህገመንግስታዊና ፀረ ዴሞክራሲያዊ አካሄድ  ለዓለም ማህበረሰብ ለማሳወቅ የሚያደርጉትን ተቃውሞ የማሰማት ሥራቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ መልእክቱን አስተላልፏል።

እንዲሁም የዴሞክራሲያዊ አስተዳደርና ህብረ ብሔራዊ ፌዴራሊዝም ሥርዓት እንዲገነባ የሚታትሩ የፖለቲካ ኃይሎች ከዎላይታ ሕዝብ ጎን በመቆም የዎላይታ ሕዝብ እየደረሰበት ያለውን ኢ-ህገ መንግስታዊ አሠራር እንዲቃወሙ ጠይቋል። 

በተጨማሪም የዎላይታ ሕዝብ ወደ ኢትዮጵያ በኃይል ከተቀላቀለበት ጊዜ ጀምሮ የነበረውን አስደማሚ ሥልጣኔ በተለያዩ ጊዜያት ሥልጣን በተቆናጠጡ የማዕከላዊ መንግስት ኃላፊዎች በከፍተኛ ግፍና ጭካኔ የመገርሰስ ሥራ ሲሰራበት መቆየቱን አስታውሷል። 

ከዚህም በላይ ለ128 ዓመታት የዘለቀው ይህ አፈናና ጭቆና እስከዛሬዋ ቀን ድረስ ከመዝለቁም በላይ የማብቂያው ጊዜ እንኳን በውል አለመታወቁን የገለጸው የዎላይታ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ግንባር  ከመላው ደጋፊዎቹ፣ አባላቱና አጋሮቹ ጋር በመሆን ሠላማዊ ትግሉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አሳውቋል።

[ad_2]

Source link

What do you think?

Aggregated by Ethiopian News Digest

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

GIPHY App Key not set. Please check settings

Oromia bank scoops international award

Oromiyaa bakkeewwan garaagaraatti humnoonni mootummaa namoota ukkaamsanii asbuutee dhabamsiisaa jiraachuun himame. – OMN