in

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ከፍተኛ አመራር አብዲ ረጋሳ ወደ ቡራዩ እስር ቤት መዘዋወራቸው ተሰማ።

[ad_1]

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ከፍተኛ አመራር አብዲ ረጋሳ ወደ ቡራዩ እስር ቤት መዘዋወራቸው ተሰማ።

ለረጅም ጊዜ በእስር ላይ የቆዩት የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ከፍተኛ አመራር አብዲ ረጋሳ ወደ ቡራዩ እስር ቤት መዘዋወራቸው ተሰማ።

በሌላ በኩል የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከኮሎኔል ገመቹ አያና ጋር የተከሰሱትን የሁለት ተከሳሾች መዝገብ መዝጋቱ ተነገሯል።

ኮሎኔል ገመቹ አያና ለአመታት ክስ ተመስርቶባቸው በግፍ በተደጋጋሚ ፍርድ ቤት ሲቀርቡ ከቆዩ በኋላ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጉዳዩን ወደ ፍትህ ሚንስቴር በመመለስ ክሱን እንደገና እንዲመለከተው ወስኖ ነበር።

ላለፉት 3 ወራት ኮሎኔሉን ጨምሮ ሌሎች ጥቂት ታሳሪዎች በፌዴራል ፖሊስ ጣቢያ ታስረው ጉዳያቸው በፍርድ ቤትም ሆነ በወንጀል ምርመራ ሳይቀርብ ቆይቷል።

የኦሮሞ ፖሊቲካ እስረኞች ጠበቆች ቡድን ጉዳዩን ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት አቅርቦ እንደነበር ጠበቃ ቱሊ ባይሳ ነግረውናል ።

በዚሁ አግባብ ፍርድ ቤቱ ፖሊስ መልስ እንዲሰጥ ትእዛዝ ቢሰጥም በመጀመሪያ ቀጠሮ ከታሳሪዎቹ መካከል ለሜሳ ታከላና ኦስማን ሃሰን ችሎት ቢቀርቡም ለምን በእስር እንደቆዩ ፖሊስ ማብራሪያ ሳይሰጥ መቅረቱን አቶ ቱሊ ባይሳ ተናግረዋል።

ፍርድ ቤቱ ፖሊስ ማብራሪያ እንዲሰጥ ሁለተኛ ቀጠሮ ለሚያዝያ 20 ከሳአት ይዞ ነበር። 

በትናንትናው እለት ፖሊስ ለችሎቱ በላከው ደብዳቤ አቶ ለሜሳ ታከለና ኦስማን ሃሰን መፈታታቸውን አሳውቋል።

ምላሹን ተከትሎ የሁለቱን የክስ መዝገብ ፍርድ ቤቱ የዘጋ ሲሆን የኮሎኔል ገመቹ ጉዳይ ግን ምላሽ አለማግኘቱን ጠበቃቸው ለኦ ኤም ኤን ገልጸዋል።

ኮሌኔሉ  አሁንም በፌዴራል ፖሊስ ጣቢያ ታስረው የሚገኙ ሲሆን እስከ አሁን እሳቸውን በተመለከተ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የሰጠው ትእዛዝ አለማከበሩን ጠበቃቸው ገልጸዋል።

በሌላ ዜና የኦነግ ከፍተኛ አመራር የሆኑት አብዲ ረጋሳ ከገላን እስር ቤት ወደ ቡራዩ መዘዋወራቸውን የድርጅቱ ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ለሚ ገመቹ ነግረውናል።

በቡራዩ ቁጥር ሶስት ፖሊስ ጣቢያ ታስረው የሚገኙ ሌሎች የኦነግ አመራሮች በተላላፊ የጉበት በሽታ ተይዘው እንደሚገኙ መዘገባችን ይታወሳል።

[ad_2]

Source link

What do you think?

Aggregated by Ethiopian News Digest

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

GIPHY App Key not set. Please check settings

Fiche-Chambalala: a look into Sidama’s unique calendar | Addis Zeybe

News: UNICEF Exec. Director visits drought-stricken Somali region; calls for urgent response to save lives of millions of children