in

የአፋር ጨው ማምረቻ ድርጅት ፈቃድ እንዳይታደስ የአፋር ክልል መንግሥት ጠየቀ






DALLOL, ETHIOPIA – JANUARY 22: A camel caravan carrying salt mined by hand is led across a salt plain in the Danakil Depression on January 22, 2017 near Dallol, Ethiopia. The depression lies 100 metres below sea level and is one of the hottest and most inhospitable places on Earth. Despite the gruelling conditions, Ethiopians continue a centuries old industry of mining salt from the ground by hand in temperatures that average 34.5 degrees centigrade but have risen to over 50 degrees. (Photo by Carl Court/Getty Images)

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በኢትዮጵያ የማዕድን ነዳጅና ባዮፊውል ኮርፖሬሽን 83 በመቶ ድርሻ የተመሠረተው የአፋር ጨው ማምረቻ አክሲዮን ማኅበር በአፋር ክልል አፍዴራ የተሰጠው የጨው ማምረት ፈቃድ እንዳይታደስ የአፋር ክልላዊ መንግሥት ጠየቀ።

ጥያቄውን ያቀረቡት የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ አወል አርባ እንደሆኑ የሪፖርተር ምንጮች ገልጸዋል።
የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ አወል ጥያቄውን ያቀረቡት ለማዕድን ሚኒስቴር መሆኑን የገለጹት ምንጮች የአፋር ጨው ማምረቻ አክሲዮን ማኅበር ላለፉት ሃያ ዓመታት በአፋር ክልል ጨው ለማምረት ሲጠቀምበት የነበረው የማዕድን ፈቃድ በመጪው ሰኔ 2014 ዓ.ም. እንደሚጠናቀቅ በማመልከት፣ የማዕድን ሚኒስቴር የማኅበሩን ፈቃድ ለተጨማሪ ጊዜ እንዳያድስ መጠየቃቸውን ገልጸዋል።

ለአክስሲዮን ማኅበሩ የተሰጠው የማዕድን ፈቃድ ጊዜ ሲጠናቀቅ ይዞታው ለክልሉ እንዲመለስ፣ በይዞታው ላይ ጨው የማምረት አዲስ የማዕድን ፈቃድ ለአፋር ልማት ድርጅት እንዲሰጥ ጥያቄያቸውን አቅርበዋል።

የፌዴራል መንግሥት የልማት ድርጅት የሆነው የኢትዮጵያ የማዕድን፣ ነዳጅና ባዮፊውል ኮርፖሬሽን በአፋር ጨው ማምረቻ አክሲዮን ማኅበር ላይ 83 በመቶ ድርሻ በመያዝ ወሳኝ ባለድርሻ ሲሆን፣ ቀሪው 17 በመቶ የሕወሓት ኢንዶውመንት የሆነው ኢፈርትና ሌሎች ባለድርሻዎች የተያዘ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ።








Source link

What do you think?

Aggregated by Ethiopian News Digest

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

GIPHY App Key not set. Please check settings

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር የኔትወርክ መጋራት ስምምነት ተፈራረመ

በሰሜን ሸዋና በኦሮሚያ ልዩ ዞን በተቀሰቀሰ ግጭት የፀጥታ ኃይሎችና ንፁኃን ዜጎች ሞተዋል