ምክር ቤቱ ከዓለም አቀፍ የልማት ማህበር ጋር በተደረጉ በአራት የብድር ስምምነቶች ላይ የተወያየ ሲሆን በድምሩ የ1 ቢሊየን 130 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር የብድር ስምምነቶች በማጽደቅ ረቂቅ አዋጆቹ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ ወስኗል።
ሁሉም ብድሮች ምንም አይነት ወለድ የማይታሰብባቸው፤ ባንኩ ብድሮቹን በማስተዳደር ረገድ ለሚሰጠው አገልግሎት 0.75% የአገልግሎት ክፍያ የሚታሰብባቸው ሆነው የ6 ዓመት የችሮታ ጊዜን ጨምሮ በ38 ዓመታት ተከፍለው የሚጠናቀቁ ናቸው ተብሏል፡፡
በተጨማሪም ምክር ቤቱ የአፍሪካ የመንገድ ደህንነት ቻርተር እና የተባበሩት መንግስታት የመንገድ ትራፊክ ኮንቬንሽን ማጽደቂያ ረቂቅ አዋጆች ላይ ተወያይቶ በሙሉ ድምጽ በማጽደቅ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፉ ወስኗል፡፡
GIPHY App Key not set. Please check settings