[ad_1]
‘’በአካባቢው አስተማማኝ ሠላም በመስፈኑ ከትግራይ ክልል የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ አገራቸው እንዲመለሱ አየሰራሁ ነው” በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ
በሱዳን የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ባወጣው መግለጫ ስደተኞቹ የመጡበት አካባቢ አስተማማኝ ሠላም የሰፈነ በመሆኑ ወደ አገራቸው የሚመለሱበትን ሁኔታ እያመቻቸሁ ነው ብሏል ።
ከቀያቸው ተፈናቅለው በአገር ውስጥና በውጭ የሚገኙ ስደተኞች ወደ መደበኛ ኑሯቸው ለመመለስ መንግስት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል ብሏል ኤምባሲው በማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገፁ ባወጣው መግለጫው፡፡
በትግራይ ክልል እየተካሄደ በሚገኘው ጦርነት በርካቶች ወደ ሱዳን መሰደዳቸው የሚታወስ ነው።
UNICEF ባወጣው ሪፖርት መሰረት 1.6 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች በግጭቱ ምክንያት ተፈናቅለዋል።
ባሳለፍነው ሳምንት አለም አቀፍ ተቋማት 90 በመቶ የሚሆኑ የትግራይ ክልል ነዋሪዎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል ሲሉ አስታውቀው ነበር ።
መንግስት በበኩሉ ከአካባቢ ደህንነት ጋር በተያያዘ የተዘጉ ውስን መንገዶች ቢኖሩም በአካባቢው የሰብዓዊ ደጋፍ አገልግሎት እንዲስፋፋ እየሰራሁ ነው ብሎ ነበር።
Related
[ad_2]
Source link
GIPHY App Key not set. Please check settings