በሱዳን ደቡባዊ ዳርፉር ግዛት በተቀሰቀሰ ግጭት የ36 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 32 ሰዎች መቁሰላቸውንም ሲጂቲኤን አፍሪካ ዘግቧል።
ግጭቱ የተከሰተው በደቡባዊ ደርፉር በሚኖሩ ፌላታ እና ቴይሻ በተሰኙ ሁለት ጎሳዎች መካከል በተፈጠረ የመሬት ይገባኛል ግጭት እንደሆነ ዘገባው ጠቁሟል።
በሱዳን ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት እና በአካባቢው በሚንቀሳቀሱ አማጺ ሀይሎች መካከል የተለያዩ ስምምነቶች ቢደረጉም በአካባቢው ጎሳን መሰረት ያደረጉ ገጭቶች በተደጋጋሚ እየተከሰቱ እንደሆነ ተገልጽል።
የአፍሪካ ህብረት የጋራ ሰላም አስከባሪ ሀይል ካሳለፍነው ጥር ጀምሮ በመውጣቱ የሱዳን ብሔራዊ ጦር አካባቢው ቢቆጣጠርም ግጭቶቹ ሊቆሙ አልቻሉም።
በዳርፉር እ.ኤ.አ 2003 በተከሰተ የጎሳ ግጭት 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ህዝብ የተፈናቀለ ሲሆን ካለፈው ዓመት ጀምሮ ደግሞ ግጭቶቹ በድጋሚ በማገርሸት ላይ እንደሚገኙ ዘገባው ጠቁሟል።
GIPHY App Key not set. Please check settings