[ad_1]
የኢፌድሪ ጠ/ሚር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ያለፉት ሦስት ዓመታት ዋና ዋና ንግግሮቻቸውን የያዘ ”ዐሻራ” የተሰኘ መጽሐፍ የምረቃ ስነስርዓት እና በኢፕድ 80ኛ ዓመት በዓል ላይ ተገኝተው ነበር።
በዚህም ወቅት ላይ የ3 ዓመታቱን ፈተናዎች በተመለከተ ንግግር አድርገዋል፡፡
ከተናገሩት መካከል ፦
” ተደጋጋሚ ችግር ያሳለፍንባቸው ያለፉት ሶስት ዓመታት ፣ በፊት ከነበሩት 10 ዓመታት ጋር ሲነፃፀሩ ቢያንስ ከጂኦ ፖለቲካ አንፃር የከፉ ጊዜያት ናቸው።
በሰሜን የገጠመንን ግጭት አንዳንዶች ከኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት፣ ከካራማራው ጦርነት ጋር ሊያነፃፅሩ ይሞክራሉ ፣ ነገር ግን ወታደርም ስለሆንኩ ከሁሉም የከፋው ግጭት ነው።
ከጣልያን ጋር ስንዋጋ በጎራዴም ቢሆን እኛ ጎራዴያችንን ይዘን እነሱም በመሳሪያቸው ተዋግተናል። በኤርትራ እና ካራማራውም እኛም እነሱም ባለን ነው የተዋጋነው።
አሁን ግን የነበረው ውጊያ የኛን ትጥቅ እና የኛን መከላከያ በማፍረስ ነው ከኛ ጋር የነበረው ወጊያ።
ባለፉት ሶስት ዓመታት ብዙ ፈተናዎች ውስጥ ሆነን በሰላሙ ጊዜ ተጀምረው መጠናቀቅ ካልቻሉ 10 ትላልቅ የስኳር ፋብሪካዎች 7ቱን አጠናቀናል፤ ሌሎች ብዙ ፕሮጀክቶችንም እንዲሁ።”
Related
[ad_2]
Source link
GIPHY App Key not set. Please check settings