[ad_1]
በማህበራዊ ሚዲያ ላይ እየተሰራጨ ያለው አሰቃቂ ግድያ በወሎ ዳዋ ጨፋ ወረዳ እንደተፈፀመ የኢትዮጵያ ሰብኣዊ መብት ኮሚሽን አስታወቀ።
በማህበራዊ ሚዲያ ላይ እየተሰራጨ ያለው አሰቃቂ ግድያ በወሎ ኦሮሞ ልዩ ዞን ዳዋ ጨፋ ወረዳ እንደተፈፀመ ማረጋገጡን የኢትዮጵያ ሰብኣዊ መብት ኮሚሽን አስታወቀ።
ኮሚሽኑ ባወጣው መግለጫ ግድያው በኢትዮጵያ አቆጣጠር በታህሳስ ወር 2014 በአማራ መንግስት የፀጥታ ሃይሎች በዳዋ ጨፋ ወረዳ ልዩ ስሙ እንቶሊ በተባለ ቦታ መፈጸሙን አረጋግጧል።
ኮሚሽኑ እንዳለው የተጎጂዎች ቁጥር ወደ 30 ገደማ ነው።
በሁለት መኪኖች ተጭነው ወደስፍራው ከተወሰዱ በኋላ በአሰቃቂ ሁኔታ እንደተገደሉ ማረጋገጡን ገልጿል።
ግድያው እጅግ በጣም አሰቃቂ በሆነ መንገድ የተፈጸመ ሲሆን ተንቀሳቃሽ ምስሉ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በስፋት እየታየ ነው።
እነዚህ የክልሉ መንግስት ሃይሎችና አብሯቸው የነበሩ የሚኒልክ አርማ የለበሱ ታጣቂዎች ብዛት ያላቸውን ሰላማዊ ሰዎችን በእቃ ጫኝ አይሱዙ ጭነው ስያመጡ በተንቀሳቃሽ ምስሉ ላይ ይታያል።
ቀጠሉና እየደበደቧቸው ከመኪናው እንዲወርዱ ካደረጉ በኋላ ጥይት አዝንበውባቸው ስጨፈጭፉ በግላጭ ታይቷል።
ፊልም እንጂ የእውነት አይመስልም። በምስሉ ላይ ገዳዮች በመኪና ጭነው ያመጧቸውን ንጹሃን እየገፈታተሩ እና እየደበደቡ ፋታ ሳይሰጡ በተኩስ እሩምታ ረሽነዋል።
ሁሉም ይተኩሳል፣ እንረጋጋ ይላል አንዱ፣ አንዱ ከሌለኛው እየተሽቀዳደመ ይገድላል፣ ለመግደል ቀድሞ ባታ የያዘውን በሚያመለክት መልኩ አበበ ና ወደዚህ እንግደላቸው የሚል ድምጽ ይሰማል፣ አንደኛው በእጁ የግድያውን ሂደት ለመምራት ይሞከራል።
ከመኪናው የወረዷቸውን እየገደሉ በማሃል በመኪና ላይ የቀሩትን እየደበደቡ በማውረድ መግደል ይቀጥላሉ።
ከገዳዮቹ መካከል አንዱ መኪና ላይ እንዴት ትተኩሳለህ መተሀኝ ነበር እኮ ሲል ይሰማል።
ከዚያም ከመኪናው ላይ አውርደው ተኩሱ ይቀጥላል፣ በማሃል አንዱ ለዚህ ጥይት አታባክን ቀስ ብሎ ተሰቃይቶ ይሙት ሲል ይሰማል።
[ad_2]
Source link
GIPHY App Key not set. Please check settings