in

“ሴት ልጆቻችሁን አግቻለው ፤ ለገበያ አቅርቤም እሸጣቸዋለው” አቡበከር ሼካው

[ad_1]

“ሴት ልጆቻችሁን አግቻለው ፤ ለገበያ አቅርቤም እሸጣቸዋለው” አቡበከር ሼካው
የቦኮሃራሙ መሪ አቡበከር ሼካው እራሱን በፈንጂ ማጥፋቱ እየተዘገበ ነው

የቦኮሃራሙ መሪ አቡበከር ሼካው ህይወቱ ሳያልፍ እንዳልቀረ ከተነገረ ወራት ቢቆጠሩም ሼካው እራሱን በፊንጂ ማጥፋቱ አሁን አነጋጋሪ ዜና ሆኖዋል።

የናይጄሪያ ፖሊስ የግለሰቡን ሞት አጣራለው ካለ ሳምንታትን ካስቆጠረ በኋላ ነው የግለሰቡን አሟሟት የሚያስረዱ መረጃዎች የወጡት።

የዜና ወኪሎች አገኘነው ባሉት መረጃ ሼካው በራሱ ላይ ፈንጂ አፈንድቶ ነው ህይወቱ አለፈ የተባለው።

የአሟሟቱ ዜና ተገኘ በተባለው የድምፅ ቅጂ የኢስዋፑ መሪ አቡ ሙስዓብ አል-ባራዊ መሆኑ ተጠርጥሯል።

አቡበከር ሼካው ላለፉት አምስት አመታት ቦኮሃራምን ሲመራ ቡድኑ ከምንግዜም በላይ አሰቃቂ የሆኑ የ አፈና እና ግድያ ወንጀሎችን የፈፅመበት ግዜ መሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ።

በ1996 ዓ.ም. 200 የሚሆኑ ሴት ተማሪዎችን ባገተበት ወቅት “ሴት ልጆቻችሁን አግቻለው ለገበያ አቅርቤም እሸጣቸዋለው” የሚለው ንግግሩ ብዙዎችን ያስከፋ ነበር ።

ታዲያ በአሸባሪነት የፈረጀችው አሜሪካ ይህን ሰው ይዞ ላመጣልኝ በ7 ሚሊየን ዶላር ሽልማት አንበሸብሸዋለው ብላ ቃል ገብታም ነበር።

የሼካው ሞት ዜና ሲሰማ ይሄ የመጀመሪያ አይደለም።

አሁንም ቢሆን የናይጄሪያ መንግስት መምቱን በተመለከተ ያለው ነገር አለመኖሩን አለም አቀፍ የዜና ምንጮች ዘግበዋል



0



0


Happy


Happy




0 %


Sad


Sad



0 %


Excited


Excited



0 %


Sleppy


Sleppy




0 %


Angry

Angry



0 %


Surprise

Surprise



0 %

[ad_2]

Source link

What do you think?

Aggregated by Ethiopian News Digest

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

GIPHY App Key not set. Please check settings

A new book explores story of exiled Ethiopian musicians in the US | Addis Zeybe

የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በግል ባንኮች የከፈቷቸው የባንክ ሒሳቦች በሙሉ እንዲዘጉ ታዘዙ