in

ማን ተጠቅሞ ማን ይጎዳ ይሆን? (እውነቱ ቢሆን) – ዘ-ሐበሻ (Zehabesha) የዕለቱ አብይ ዜና | ሰበር ዜና | አስተያየትና ትንታኔ

[ad_1]

በቁማርተኛ ፖለቲከኞች ልባችሁ ያልቆሸሸ አማራወችና ትግሬወች ሆይ፦

እነዚህን ከስር የተጠቀሱ ሁለት ዩ ቲዩቦችን ተመልከቱና  ማን ጥፋተኛ እንደሆነ ራሳችሁ ፍረዱ፡፡ ከሹምባሹ የዜናዊ አስረስ ልጅ ከመለስ ዜናዊ ጀምሮ ባንዳነትና ከሀዲነት የተጠናወታቸው ከትግራይ የወጡት የህወሀት መሪወች የተወሰነውን የትግራይ ህዝብ በከሉት፡፡ ለዚህ አሁን ላለበት ሁኔታም አበቁት፡፡ ጉዳዩ ብዙ ዝርዝሮች ያሉት ስለሆነ እዚህ ላይ አላነሳውም፡፡ እዚህ ላይ በጣም በአጭሩ የማነሳው ለሽህ አመታት ለኢትዮጵያ ዋልታና ማገር የነበረው የአማራና የትግሬ ህዝብ ለምን ለመገዳደል በቃ የሚለውን ጠቆም ለማድረግ  ብቻ ነው፡፡

በቪድዮ ቁጥር አንድ የተግሬ ወጣቶች እንዲህ እያሉ ሲጨፍሩ ይታያሉ፡፡

“አንተ ጀግና የትግሬ ታጋይ

አሳደህ በለው ያን ሞኝ አማራ”

ቪድዮ ቁጥር አንድ፦ https://www.youtube.com/watch?v=IgElvgA75cs

በቪድዮ ቁጥር ሁለት  አማራው ታላቁን የኢትዮጵያ ንጉስ አጼ ዮሀንስን በአክብሮት በዘፈን ይዘክራቸዋል፡፡

ቪድዮ ቁጥር ሁለት፦ https://www.youtube.com/shorts/jl0yiLWojzE

ዘፈኑም እንዲህ ይደመጣል፡፡

“” ለዚች አገርማ ጀግና ካልሞተማ

ምን ይበል ዮሀንስ የቀረው መተማ””

ሁለቱንም ቪድዮ ደጋግማችሁ ተመልከቷቸው፡፤ ምን ተሰማችሁ???

ያለፉትን 40 አመታት የወልቃይትና ራያን “”የታሪክ ሸፍጥና የፖለቲካ ቁማር ጨዋታውን” ለጊዜው ወደጎን እንተወውና ለምን ይህ ሆነ?? ማንስ አደረገው? ዉጤቱስ ወዴት ያመራል …ወዘተ ለሚሉት ጥያቀወች ማንም መልስ ሊሰጥ አይችልም፡፤ (ለጊዜው ነገሩን ወደጎን እንተወዉ ያልኩበት ዋና ምክንያት ኦሮሙማም ሆነ ሌላው ሌላው አዳከረ አላዳከረ ነገሩ ስለማይጠቅም ብቻ ሳይሆን እውነትን ማጥፋት ስለማይቻል ነው፡፡)

አንድ ቁም ነገር ግን አለ፡፡ ርስት ጉልትነታቸው የአማራው የሆኑት እነዚህን መሬቶች ለመቀራመት ከውስጥም ከውጭም የሚቋምጡት ሀይሎች ብዙ ናቸው፡፡ አማራው አሁን የሚገኘው “ብአደን” በሚባል በፊት የመርዘኛውና የባንዳው ወያኔ አሁን ደግሞ የተረኛውና ጭራቁ አብይ አህመድ አሊ የሚመራው የጅብ መንጋ የታጎረበት የኦሮሙማ አሽከር ሆኖ እንደ አህያ ሁሉም ጌቶቹ እየተፈራረቁ የሚጭኑትን ሁሉ በሚጫነው በዚህ ገልቱ ስብስብ ተሸብቦ፣ ታውሮና የፊጥኝ ታስሮ የሚዋከብበት ወቅት ላይ ነው ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ድሬዳዋ ዛሬም ሳትረጋጋ ዋለች

አሁንም ሆነ ወደፊት የእገሪቱ ችግሮች የሚቀዱት መሬቶቹ እጅግ ለምና ለሰፋፊ አግሮ ኢንዱትሪ ከፍተኛ ምርታማነት አመቺ መሆናቸው በጥናት ከተረጋገጡት ከነዚሁ ለም መሬቶች ዙሪያ በሚካሄደው የቁማር ጨዋታ ነው፡፡

ስለመሬቶቹ እጅግ ለም መሆን የተሰራውን አዋጭ ጥናት ወያኔ በጠረጴዛ መሳቢያ ውስጥ ቆልፎበታል፡፡

እስካሁን የሆነው ሁሉ እንደዚያ ሆኖ ካለፈ በኋላ አሁን ላይ በዚህ ደረጃ ለደረሰው ጥላቻና መጠፋፋት ማን ነው ተጠያቂው?? አሁንስ ምን እየሆነ ነው? ለምን?? ወደፊትስ አማራና ትግሬ እንደዱሮው ሊኖሩ ይችሉ ይሆን?? ካልሆነስ ማን ተጠቅሞ ማን ይጎዳ ይሆን???

መቼም ቢሆን ህዝብ ህዝብ ነው፡፤ ፖለቲከኛም ፖለቲከኛ !!

 

[ad_2]

Source link

What do you think?

Aggregated by Ethiopian News Digest

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

GIPHY App Key not set. Please check settings

 “የዛሬው የአገራችን ሁኔታ ከዲፕሎማሲ አንፃር” በሚል አርዕስት ስር በአቶ  ባይሳ ዋቅ-ወያ ለቀረበው ገለጻ የተሰጠ ሀተታዊ መልስ! – ዘ-ሐበሻ (Zehabesha) የዕለቱ አብይ ዜና | ሰበር ዜና | አስተያየትና ትንታኔ

አካፋን አካፋ ብሎ ለመጥራት የመቸገር የፖለቲካ ባህል – ጠገናው ጎሹ – ዘ-ሐበሻ (Zehabesha) የዕለቱ አብይ ዜና | ሰበር ዜና | አስተያየትና ትንታኔ