[ad_1]
ዓለም አቀፉ የረድኤት ተቋም በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የህጻናት አድን ፈንድ ዩኒሴፍ እንዳስታወቀዉ ሀብታም ሀገራት የተያዘዉ ዓመታት ሳይገባደድ በፍጥነት የኮሮና ቫይረስ ክትባትን ለደሃ ሀገራት የማይልኩ ከሆነ ከፍተኛ ብክነት ያጋጥማል ሲል አስጠንቅቋል፡፡
ዩናይትድ ኪንግደም እና ሌሎች ሀገራት የተረፋቸዉን ክትባት ለመለገስ ቃል የገቡ ሲሆን በቶሎ እንዲለግሱ ተጠይቀዋል፡፡የዩኒሴፍን ቅስቀሳ አሜሪካዊቷ ድምጻዊት ቢሊ ኢሊሽ እና ዴቪድ ቤካምን ጨምሮ ድጋፋቸዉን ቸረዉታል፡፡
ዝነኞቹ እንግሊዝን ጨምሮ የቡድን ሰባት የበለፀጉት አገራት ደብዳቤ ያስገቡ ሲሆን እስከ ነሐሴ ወር ድረስ ሀገራቱ ካላቸዉ ክትባቶች 20 በመቶዉን እንዲለግሱ የሚጠይቅ ነዉ፡፡ቤካም እንደተናገረዉ ወረርሽኙ በየትኛዉም ቦታ እስካልጠፋ ድረስ አይቆምም ሲል አስታዉቋል፡፡
የእንግሊዝ የጤና ጥበቃ ጸሀፊው ማት ሀንኩክ ወደ ዉጪ ሀገራት ክትባቱን ከመላካችን በፊት በሀገር ውስጥ ህፃናት ክትባቱን እንዲወስዱ ቅድሚያ እንሰጣለን ሲሉ ተናግረዋል
Related
[ad_2]
Source link
GIPHY App Key not set. Please check settings